loading
የመምህራን አገልግሎት ኮሚሽን ሊቋቋም ነው፡፡

የመምህራን አገልግሎት ኮሚሽን ሊቋቋም ነው፡፡

በመምህራን ጉዳዮች ላይ የሚሰራ የመምህራን አገልግሎት ኮሚሽን ሊቋቋም መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሃንስ በንቲ የትምህርትን ጥራት ለማሻሻል የትምህርት ሙያተኛውን ኑሮ ማሻሻል እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለዚህም ዘርፉን ለመምራት ከሲቪል ሰርቪስ የተለየና ተጠሪነቱም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆነ ኮሚሽን እንዲቋቋም መጠየቃቸውን ነው የተናገሩት።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዝግጅትና ትግበራ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ፥ ፍኖተ ካርታው አጠቃላይ የትምህርትና ስልጠና ስርዓቱን እንደሚፈትሽ ነው ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በጥናት ላይ ተመስርቶ የመምህራንን ጥቅማ ጥቅም ለማስከበር በዝርዝር እንደሚሰራ ጠቅሰው፥ ኮሚሽኑን ለማቋቋም የህግ ማዕቀፎች እየተዘጋጁ መሆኑንም ገልፀዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው የትምህርት ማኅበረሰቡን አደረጃጀት፣ ስነ ምግባር እና ጥቅማ ጥቅሙን በሚመለከት ነጻ በሆነ አካል ተጠንቶ ከመቋቋሙ አስቀድሞ በሚመለከታቸው አካላት ሀሳብ ይሰጥበታል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *