loading
የሊቢያ ጦርነት ጦሱ ለቱኒዚያዊያንም ተርፏል፡፡

የሊቢያ ጦርነት ጦሱ ለቱኒዚያዊያንም ተርፏል፡፡

በሊቢያ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት በርካታ የሀገሪቱ ዜጎች ወደ ጎረቤት ቱኒዚያ እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል፡፡

የነዚህ ሊቢየያዊያን መፈናቀል እና በሰው ሀገር መኖር እነሱን ብቻ ሳይሆን የተጠለሉባትን ቱኒዚያንም ዜጎቿ የኑሮ ጫናእንዲበረታባቸው አድርጓል ነው የተባለው፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው በሊቢያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኙ የቱኒዚያ ከተሞች ከትሪፖሊ እና አካባቢዋ በተሰደዱ ሰዎች በመጨናነቋ ምክንያት የቤት ኪራይ ዋጋ አልቀመስ ብሏል፡፡

ነዋሪዎች እንደሚናገሩት በቀን ከ40 እስከ 80 የቱኒዚያ ዲናር ኪራይ ይጠየቃሉ፡፡ ይህም ወደ 20 በመቶ የሚሆን የዋጋ ጭማሪ መሆኑ ነው፡፡

የጄኔራል ሀፍታር ታማኝ ወታደሮች ትሪፖሊን ለመያዝ በሚያደርጉት ውጊያ የተነሳ ሊቢያዊያን ኑሮም በሰቀቀን  የተሞላ ሀኗል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም የተኩስ አቁም እንዲደረግ ቢጠይቅም ብዙም ሰሚ አይመስልም ነው የተባለው፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *