loading
የህዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ኢትዮጵያዊያን ሊረባረቡ ይገባል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ7፣ 2012  የህዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ኢትዮጵያዊያን ሊረባረቡ ይገባል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩይን ያሉት ሁለተኛው ሃገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ በተገኙበት ወቅት መሆኑን ነው። በፕሮግራሙ ስነሰርዓት ችግኝ በመትከል የተሳተፉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የለውጡ ኃይል ወደ ስልጣን ሲመጣ የገባውን ቃል ለመፈፀም ከፍተኛ ጥርት እያደረገ ይገኛል ብለዋል። በሁለተኛው ሃገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር ለመትከል የታቀደው አምስት ቢሊዮን ችግኝ በሐምሌ ወር ውስጥ ማሳካት ተችሏልም ብለዋል።

ኢትዮጵያዊያን ችግኝ ለመትከል ከፍተኛ ርብርብ እንዳደረጉ ሁሉ ሀገሪቱን በሁሉም ዘርፍ የምስራቅ አፍሪካ ፋና ወጊ ለማድረግ እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ትብብር እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ከማይጠቅም ከፋፋይና የኔ ብቻ ከሚል አስተሳሰብ በመላቀቅ የሀገሪቱ ህዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መላ ኢትዮጵያዊያን ሊረባረቡ እንደሚገባ አሳስበዋል። መንግስት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በቁርጠኝት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህ እውን እንዲሆን ህዝቡ ያልተቆጠበ ድጋፍና እግዛ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *