loading
የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ የመክፈቻ ስነ ሥርአት ተካሄደ ።

የጋራ ምክር ቤቶቹ 5ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።
የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የምክር ቤቶቹን የጋራ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት ባለፈው ዓመት ሀገሪቱ በገባችበት የለውጥ ሂደት አሳሳቢ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነበረች ብለዋል፡፡
ገዥው ፓርቲ ግምገማ በማድረግ ችግሮቹን በመፍታቱ በሃገሪቱ ለውጦች እየተመዘገቡ ናቸው ያሉት ፕሬዝዳንቱ አዲሱ አመራር ለህዝብ ጥያቄ በመገዛት ወሳኝ የለውጥ ምዕራፍ ላይ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ይቅርታና መደመርን መሰረት ያደረጉ ለውጦች በተግባር ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ፤ በርካታ እስረኞች ተፈተዋል ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፣
ነፍጥ አንስተው ከነበሩ ሃይሎች ጋር ውጤታማ ውይይት መደረጉን የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ለሀገራቸው በያገባኛል በጋራ የሚሰሩበት ሁኔታ መፈጠሩንም ገልጠዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተጋረጠብን አዳጋ መረን የለቀቁ እንቅስቃሴዎች እየታዩ ሲሆን በዚህም ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ተፋናቅለዋል፣ ንብረት ወድሟል ነው ያሉት፡፡
በህግ የበላይነት የማይመራ ሀገር ውጤቱ ግጭት ፤ ጥፋትና መበታተን ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ለዚህም የዴሞከራሲ ተቋማትን እና አሰራርን ማጠናከር አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ገልጠዋል፡፡
የሀገሪቱ 65 በመቶ ያህል ለሆነው ወጣት መንግስት ለስራ እድል ፈጠራ እንደሚሰራ ገልጠው ሀገራዊ ደህንነት ትኩረት እንደሚሰጥም አስታውቀዋል በንግግራቸው።
የመንግስት ብድር ከተቀመጠለት ገደብ በላይ እንዳያድግ እንዲሁም የፈጠራና የቴክኖሎጂ ሞዴሎችን ለማፋጠን ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ጠቁመው; የድንበር አካባቢ ንግድ ፍታዊ አና ህጋዊ ስርዓት እንዲከተል በማድረግ ከውጭ ሀገራት ጋር የንግድ ድርድር በማድረግ መንግስት ሃለፊነቱን እንድሚወጣም አስታውቀዋል።
አሁን ላይ በሀገሪቱ ያለውን የህዝብ የምግብ ፍጆታ ለመሸፈን እና የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ለማቅረብ የክትተልና ድጋፍ ስርዓቱ ተጠናክሮ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ፣ የመስኖ ልማትን ማስፋፋት፣ የምርት ግብዓት አቅርቦትን የማሳደግ ስራዎች ይሰራሉም ብለዋል።
ፕርዚዳንቱ በንግግራቸው የዴሞከራሲ ስርዓት ስር እንዲሰድ ሰላማዊ አቅጣጫዎችን መከተል እንደሚያስፈልግ ተናግረው ግጭት ሞት ስደትና መፈናቀል ለመከላከል ፈጥነን መስራት አለብን ብለዋል።
አንድነትና ህብርታችን የይስሙላ ሳይሆን የቆየ ስር የሰደደ ባህላችን ነው ሉት ፕርዚዳንቱ እንደማሳያ
የጋሞ አባቶች ያከናዎኑትን እርቅ ተግባር ጠቅሰዋል። ዜጎች ለሰላም ለአንድነት እና የህግ የበላይነት በጋራ ሊቆሙ እንደሚገባም ተናግረዋል ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *