loading
የህዝብና ቤት ቆጠራዉ  ከማንነት ጋር እንደማይገናኝ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ገለጸ፡፡

የህዝብና ቤት ቆጠራዉ  ከማንነት ጋር እንደማይገናኝ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ገለጸ፡፡

ግጭት ያለባቸውን አካባቢዎችና የተፈናቀሉ ዜጎችን ያማከለ ቆጠራ ለማካሄድ ዝግጅት ተደርጓል ብሏል፡፡

መጋቢት 29 በሚጀመረው ግጭት ያለባቸው አካባቢዎችና የተፈናቀሉ ዜጎችን ያማከለ ቆጠራ እንደሚካሄድ አስታወቋል፡፡

ግጭት ያለባቸው አካባቢዎችንና የተፈናቀሉ ዜጎችን ጉዳይ በተመለከተ እያንዳንዱ ክልል ከለውጡ በኋላ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ ከሁለት ወራት በፊት ስብሰባ ተደርጎ መገምገሙን በኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነትና መረጃ አሰባሰብ ዳይሬክተር አቶ ሳፊ ገመዲ  ለኢቢሲ ገልጸዋል፡፡

በዚህም ሁሉም ክልል የየራሱን ሪፖርት ካቀረበ በኋላ፣ የቆጠራ ኮሚሽኑ መሰረታዊ ነጥቦች ላይ በሰፊው ውይይት አድርጎ ውሳኔ ማስተላለፉን ኃላፊው አመልክተዋል፡፡

በዚህም ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የህዝብና ቤት ቆጠራውን ለማካሄድ እንደ አማራጭ ክልሎች በአስቸካይ ተነጋግረው ችግሮችን በፈቱባቸው አካባቢዎች የቆጠራ ካርታ መሰራቱንም ገልጸዋል፡፡

አቶ ሳፊ እንደሚሉት ክልሎች ችግሩን መፍታት ባልቻሉባቸውና የቆጠራ ካርታ ባልተሰራባቸው አካባቢዎች ‘’ልዩ የቆጠራ ቦታ’’ ‘’Special Enumeration area’’ ተብሎ ተይዞ ቆጠራው ይካሄዳል፡፡

በግጭቶቹ ምክንያት ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን በተመለከተ በተመሳሳይ ውይይት ተደርጎ የተፈናቃዮች ብዛትና ያሉበት ሁኔታ መለየቱም ተመልክቷል፡፡

በዚህም የግጭቶቹን መንስኤ በመለየት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀድሞ ቦታቸው ተመልሰዋል፡፡

ወደ ቀያቸው ያልተመለሱ ዜጎችን ለመመለስ ክልሎች ከፌዴራል መንግስት ጋር በትብብር እየተሰራ ይገኛል፡፡

የማንነት ጥያቄን በተመለከተ የህዝብና ቤት ቆጠራ ከማንነት ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነም ኤጀንሲው ገልጿል፡፡

በዚህም ማንኛውም ሰው ወይም አካል የማንነት ጥያቄውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ማቅረብ እንደሚችልና ከመቆጠር የማያግድ መሆኑም ተገልጿል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *