loading
ዛሬ ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናግዳል

ዛሬ ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናግዳል

አርትስ ስፖርት 17/04/2011

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ2ኛ ሳምንት በአዲስ አበባ ስታዲየም በኢትዮጵያ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መካከል ሊደረግ የነበረው ጨዋታ ዛሬ በተስተካካይ መርሃግብር 11፡00 ላይ ይከናወናል፡፡ በሁለቱም ቡድኖች መካከል የአንድ ነጥብ ልዩነት ብቻ መኖሩ፤ የጨዋታው ፉክክር ከፍ ይላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ጨዋታው በአርቢትር አሸብር ሰቦቃ ይመራል ተብሏል፡፡

9፡00 ላይ እደሳ በተደረገለት የድሬዳዋ ስታዲየም በሊጉ አራት ነጥብ የሰበሰበው ድሬዳዋ ከነማ አንድ ድል ብቻ ያስመዘገበውን ደቡብ ፖሊስ ያስተናዳል፡፡

በነገው ዕለት እንዲሁ በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርስ ሁለት የፕሪምየር ሊግ መርሃግብሮችን ብቻ ከከወነው ጅማ አባ ጅፋር ጋር ሰገናኝ ግጥሚያው በአርቢትር ብሩክ የማነ ብርሃን ይመራል፡፡ ሁሉቱ ቡድኖች ባለፈው ዓመት ለሻምፒዮንነት ሲፎካከሩ ከርመው፤ የጅማው ቡድን በግብ በልጦ የሊጉን ዋንጫ አንስቷል፡፡

አዲስ አበባ ላይ በሚደረጉት ሁለቱም ጨዋታዎች አስቀድሞ የሰላም አምባሳደር እናቶች መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው በተስተካካይ ጨዋታ በባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ባህር ዳር ከነማ ከ ስሑል ሽሬ ጋር እንዲሁም በትግራይ አለምአቀፍ ስታዲየም መቐለ 70 እንደርታ ከ ፋሲል ከነማ እንዲሁም በሶዶ ስታዲየም ወላይታ ድቻ ከ ሲዳማ ቡና ሊያደርጉት የነበረው ፍልሚያ ለሌላ ጊዜ ተላልፈዋል፡፡

ሀዋሳ ከነማ ሁሉን የሊግ ግጥሚያዎች በማከናወን በ14 ነጥቦች ሲመራ፤ ፋሲል ከነማ፣ ቡና እና ባህር ዳር ከነማ በእኩል 11 ነጥቦች ከሁለት እስከ አራት ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *