loading
…ዓረና ትግራይና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲዎች ውህደት ለመፍጠር የሚያችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

…ዓረና ትግራይና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲዎች ውህደት ለመፍጠር የሚያችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

አርትስ 16/02/2011

ፓርቲዎቹ አብረው ለመስራትና ወደ ውህደት ለመሸጋገር የሚያስችላቸውን ስምምነት በትላንትናዉ  እለት በአዲስ አበባ  ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱንም የዓረና ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጎይቶም ፀጋይና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር  ምክትል ሊቀ መንበር ኢንጂነር ግደይ ዘርአፅዮን ናቸዉ የከወኑት፡፡

የፓርቲዎቹ ምክትል ሊቀ መንበሮች በሰጡት የጋራ መግለጫ፥ ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉአላዊነት ፓርቲና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲ የሀገሪቱ ህግ በሚፈቅደው መሰረት እስከ ውህደት የሚደርስ ትስስር ለመፍጠር ሲወያዩ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

መርሃ ግብሮቻቸውን ተለዋውጠው ካጠኑ በኋላ ለድርድር እንዲቀርቡ ባደረጉት ስምምነት መሰረት የሁለቱም ፓርቲዎች ተወካዮች ተከታታይ ውይይት አድርገው በርካታ የፖሊሲ ነጥቦች ላይ ከስምምነት መድረሳቸውንም ገልፀዋል።

ዓረና ትግራይና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ጠንካራ አማራጭ ሆነው ለመቅረብ ከትብብር ጀምሮ ወደ ውህደት ለመሸጋገር የሚያስችላቸው ስምምነት ላይ መድረሳቸውም

ትግራይ ህዝብ ትልቅ ድል ነው ብለዋል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *