loading
ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆኑ

ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆኑ

አርትስ 22/02/2011

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት 5ኛ ዙር 4ኛ የስራ ዘመን 4ተኛ መደበኛ ጉባዔውን  አካሂዷል፡፡ በጉባዔውም / መዓዛ አሸናፊ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ ወስኗል፡፡ በምክትል ፕሬዝዳንትነትም አቶ ሰለሞን አረዳ ተሹመዋል፡፡

ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ማን ናቸዉ?

/ መዓዛ አሸናፊ ተወልደው ያደጉት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ነው፡፡ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉትም በአሶሳ ከተማ ነው፡፡ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞበአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ወስደዋል፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በኢንተርናሽናል ሪሌሽንስ  አግኝተዋል፡፡ ከአሶሳ ወጥተው አዲስ አበባ ከተማን ለመጀመሪያጊዜ የረገጡት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ለመማር ተመድበው በመጡበት ጊዜ ነው፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ መጀመሪያ ወደ ሥራው ዓለም የቀላቀሉት ንግድ ሚኒስቴር ነው፡፡ ንግድሚኒስቴርን ከለቀቁ በኋላ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ሠርተዋል፡፡ ብዙም ያልገፉበትን የዳኝነት ሥራ ለቀው በሕገ መንግሥት ኮሚሽን ውስጥ ሠርተዋል፡፡ በተለይ በሕገ መንግሥት ኮሚሽንመሥራታቸው ይበልጥ የሚታወቁበትን የሴት የሕግ ባለሙያዎች ማኅበርን ለመመሥረት ዕድል ያገኙበት ነበር፡፡ እንደ ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ ያሉ ድርጅቶችም ሠርተዋል፡፡  11 ሴቶች አደራጅነትየተቋቋመው የእናት ባንክ ቦርድ ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል፡፡ 

በምክትል ፕሬዝዳንትነት የተመረጡት አቶ ሰለሞን አረዳ ደግሞ የተወለዱት ኦሮሚያ ክልል ገርበ ጉራቻ በተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ከፍተኛ የህግ አማካሪ በመሆን ሲሰሩ የቆዩ፤ ዘ ሄግ በሚገኘው የአለም አቀፍ ገላጋይ ፍርድ ቤት የሰሩና በሌሎች የአለም አቀፍና የሃገር በቀል ተቋማትከ20 አመት በላይ ያገለገሉ ናቸው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *