loading
ወይዘሮ ሎሚ በዶ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ በመሆን በዛሬው እለት ተመርጠዋል።

አርትስ 28/01/2011
ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው 4ኛ ዓመት 5ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነው አዲስ አፈ ጉባዔ የመረጠው።
በዚህም መሰረት የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ በነበሩት በአቶ እሸቱ ደሴ ምትክ ወይዘሮ ሎሚ በዶ አፈ ጉባዔ በመሆን ተመርጠዋል።
የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ነበሩት አቶ እሸቱ ደሴ ተደራራቢ የስራ ሀላፊነት ስላለባቸው ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉም ተገልጿል።
አቶ እሸቱ ለነበራቸው ቁርጠኛ አመራር እና ተሳትፎም በክልሉ መንግስት እና በጨፌው ስም ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *