loading
ኮንጓዊው የኖቤል አሸናፊ ሽልማቱ በግጭት ሳቢያ ለተጎዱ ሴቶች መታሰቢያ ይሁንልኝ አሉ

ኮንጓዊው የኖቤል አሸናፊ ሽልማቱ በግጭት ሳቢያ ለተጎዱ ሴቶች መታሰቢያ ይሁንልኝ አሉ

የፅንስና ማህፀን ስፔሻሊስቱ ዶክተር ዴኒስ ሚኩዌጌ ባለፈው ጥቅምት ወር ያገኙትን የሰላም የኖቤል ሽልማት በዓለም ዙሪያ በግጭት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ሴቶች መታሰቢያ ይሆን ዘንድ አበርክተዋል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው ሙኩዌጌ ይህን ያደረጉት መላው ዓለም ለችግሩ ጆሮ እንዲሰጥ ለማሳሰብና የጉዳቱ ሰለባዎችም የሚያስብላቸው ሰው ከጎናቸው እንዳለ እንዲያውቁ ነው፡፡

በእርስበርስ ጦርነት ወቅት ከሁሉም በላይ ተጎጅዎች ሴቶች ናቸው የሚሉት ዶክተር ሙኩዌጌ በሀገሬ ከ20 ዓመት በላይ የታዘብኩትም ይህንኑ ነው ብለዋል፡፡

ዶክተር ሙኩዌጌ በኮንጎ ደቡባዊ ኪቩ ከተማ ፓኒዝ ሆስፒታልን አቋቁመው በእርስበርስ ግጭት  ምክንያት የመደፈር ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ህክምን እና የስነ ልቦና ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

ለዚህ በጎ ምግባራቸውም ዓለም አቀፉ ኖቤል ኮሚቴ በቅርቡ ከኢራቃዊቷ የሰብዓዊ መብ ተሟጋች ናዲያ ሙራድ ጋር የ2018 ተሸላሚ አድርጓቸዋል፡፡

ዶክተር ሙኩዌጌ ሽልማቱን ካበረከቱ በኋላ እናንተ የጥቃት ሰለባ ሴቶች ሆይ በዚህ መታሰቢያ አማካይነት  ልነግራችሁ የሚፈልገው መልእክት ከእንግዲህ ዓለም ድምፃችሁን ሰምቶ ዝም እንደማይላችሁ ነው ብለወዋል፡፡

ዶክተር  ሙኩዌጌ ባበረከቱት ሰብዓዊ ተግባር ከአሁን ቀደምም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሽልማቶችን ያገኙ ለሞያቸው ታላቅ ክብር የሚሰጡ ሰው ናቸው፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *