loading
ኪም ጆንግ ኡን ለውጭ ሀገር ጋዜጠኞች ጥያቄ መልስ ሰጡ፡፡

ኪም ጆንግ ኡን ለውጭ ሀገር ጋዜጠኞች ጥያቄ መልስ ሰጡ፡፡

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሰሜን ኮሪያው አቻቸውን የኪም ጆንግ ኡንን ስብሰባ ለመዘገብ ከ40 ሀገራት የተውጣጡ 3 ሺህ ጋዜጠኞች ቬትናም ገብተዋል፡፡

ዘጋርዲያን እንደዘገበው ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን በታሪካቸው ከውጭ ሀገር ጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ታይተዋል፡፡

በመጀመሪያው  ዙር ሁለቱ መሪዎች ሲንጋፖር ላይ ሲገናኙ ጋዜጠኞች ተሰብስበው የጥያቄ ናዳ ቢያወርዱም ለአንዳቸውም መልስ አልሰጡም ነበር፡፡

በአሁኑ ውይይት ግን ከዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኛ በድንገት የተሰነዘረላቸውን የመጀመሪያ ጥያቄ ረጋ ባለ መንፈስ መለልሰዋል፡፡

ጥያቄው “የአሁኑ ድርድር ውጤት እንደሚያመጣ እርግጠኛ ነዎትን?” የሚል መንፈስ ነበረው፡፡ ኪም ሲመልሱም “ነገሮችን ቀድሜ መተንበይ ባልችልም፤ ደመነፍሴ ግን ሁሉም ነገር መልካም እንደሚሆን ይነግረኛል” ብለዋል፡፡

ከሌሎች ጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምልስም  “ከትራምፕ ጋር ስለ ሊውክሌር ጦር መሳሪያ ቅነሳ ለመደራደር ፈቃደኛ ባልሆን ኖሮ እዚህ አታገኙኝም ነበር”  ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው “ግሩም መልስ ነው የተሰጠኸው” በማለት በኪም መልስ መደሰታቸውን እዛው ነግረዋቸዋል፡፡

ጋዜጠኞቹ የመጨረሻው ቀን ውይይት ከመጀመሩ በፊት ሁለቱ መሪዎች ጋር እንዲገናኙ ተፈቅዶላቸው ነው ጥያቄውን ያቀረቡት፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *