ኩባዊያን የህክምና ባለ ሞያዎች ኮቪድ 19 የመዋጋት ጥረተን ነለማገዝ ጊኒ ቢሳዉ ገቡ::
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 ኩባዊያን የህክምና ባለ ሞያዎች ኮቪድ 19 የመዋጋት ጥረተን ነለማገዝ ጊኒ ቢሳዉ ገቡ:: አስራ አንድ ዶክተሮችን ጨምሮ 21 አባላት ያሉት የህክምና ቡድኑ ወደ ኮናክሪ ያቀናው የጊኒ ቢሳዉ መንግስት ቫይረሱን ለመግታት ባስተላለፈው የእገዛ ጥሪ ነው ተብሏል፡፡ ይህም መንግስት ቫይረሱን ለመዋጋት ከሚከተላቸው ስትራቴጂዎች አንዱ መሆኑን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡ አፍሪካ ኒውስ ባለስልጣናቱን ጠቅሶ እንደዘገበው ኩባ ከአሁን ቀደም ጊኒ ቢሳዉ የኢቦላ ቫይረስ ወረረሽኝ ሲያጋጥማት ተመሳሳይ ድጋፍ አድርጋላታለች፡፡ በአሁኑ ጊዜ 3 ሺህ የሚሆኑ ኩባዊያን የህክምና ባለ ሞያዎች አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅን ጨምሮ በ28 ሀገራት ተሰማርተው የኮሮናቫይረስን ስርጭት የመግታት ስራ እያገዙ ይገኛሉ፡፡ የጊኒ ቢሳዉ መንግስት የባለሞያዎቹን እገዛ አድንቆ ኩባ ለነፃነታችን ስልታገል ከጎናችን እንደነበረች ስናታውስ የአሁኑ ድጋፍም ሁለቱ ሀገራት ምን ያህል ወዳጆች እንደሆኑ ያሳያል ብሏል፡፡