loading
ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ 18 ሺህ 400 የአፍሪካ ስደተኞች ሞተዋል አልያም ጠፍተዋል ተባለ

አርትስ 23/02/2011

 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአለም የፍልሰተኞች ተቋም IOM ሪፖርት እንደሚያመለክተዉ 16 ሚሊዮን ስደተኞች መነሻቸዉን ከአፍሪካ ያደረጉ ናቸዉ፡፡

ከነዚህ ስደተኞች ዉስጥ 18 ሺህ 400 የሚደርሱት ከስደት መዳረሻዎች ሳይደርሱ በጉዞ ላይ ህይወታቸዉ አልፏል አልያም ጠፍተዋል ይላል የአለም የፍልሰተኞች ድርጅቱ ሪፖርት፡፡

አሶሼትድ ፕሬስ ከአለም ፍልሰተኞች ተቋም ጋር በመሆን ባደረገዉ ጥናት በ2015 የሜዲትራኒያን ባህር በማቋረጥ ላይ ከነበሩ የአፍሪካ ስደተኞች ዉስጥ 800 የሚደርሱት የተሳፈሩበት ጀልባ በመስጠሙ ምክንያት መሞታቸዉ ተረጋግጧል፡፡

ይሁን እንጂ ጣልያን ከ2015 ወዲህ ወደ ሃገሪቱ ለመግባት በሚደረገዉ ጥረት የሚሞቱና የሚጠፉ ስደተኞችን የማፈላለግ ስራዉን በማቆሟ የሟቾቹ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ በአለማችን ከ60 ሺህ በላይ ስደተኞች በጉዞ ላይ ሞተዋል ወይም ጠፍተዋል ተብሏል

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *