loading
ከአፍሪካ ፖሊዮ ቫይረስ በመጥፋቱ የጤና ሚኒስትሯ የእንኳን ደስላችሁ መልእክት አስተላለፉ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 20፣ 2012 ከአፍሪካ ፖሊዮ ቫይረስ በመጥፋቱ የጤና ሚኒስትሯ የእንኳን ደስላችሁ መልእክት አስተላለፉ፡፡ የአለም ጤና ድርጅት አፈሪካ ከፖሊዮ ነጻ መሆንዋን መግለጹን ተከተሎ ነዉ ፖሊዮን ለማጠፋት ለሰሩት የጤና ባለሞያዎች ለማህበረሰብ መሪዎች እና አባላት ወላጆችና አሳዳጊዎች እነዲሆም ለአጋር አካላት በሙሉ እንኳን ደስ አለን ብለዋል፡፡ አፍሪካ የዋይልድ ፖሊዮ ቫይረስ መጥፋት ማረጋገጫ የሆነዉን የምስክር ወረቅ መቀበሏንም ዶክተር ሊያ ገልጸዋል፡፡ የአህጉሪቱ ከፖሊዮ ነጻ መባል ለ30 ዓመታት ፖሊዮን ለማጥፋት የተካሄደው ዘመቻ ወሳኝ እርምጃ ነውም ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ፖሊዮ ዓለም ላይ በአፍጋኒስታን እና ፓኪስታን ብቻ እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *