loading
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝና ከምስራቅ ወለጋ ዞን አጎራባች ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት የባንክ ሂሳብ ተከፈተ፡፡

አርትስ 22/01/2011 ዓ.ም

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከማሺ ዞን እና በምስራቅ ወለጋ ዞን ስር ከሚገኙ አጎራባች ወረዳዎች ውስጥ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከ20 በላይ የዜጎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ከንብረትና ቄዬያቸው የተፈናቀሉትም ከ70ሺ በላይ ደርሷል፡፡

ከአራት ቀናትና ከዛ በላይ በእግራቸው በመጓዝ ነቀምቴ ከተማ የደረሱት እነዚህ ተፈናቃዮች በመምህራን ኮሌጅ፣ በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ፣ በነርሲንግ ኮሌጅና በወለጋ ዩኒቨርሲቲ እንዲጠለሉ ተደርጓል፡፡

የነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች የምግብና አልባሳት ድጋፍ እያደረጉላቸው ሲሆን፣ የመንግስት አካልም ችግሩን ለመቋቋም እየሰራ መሆኑን የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታከለ ቶለሳን ጠቅሶ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ገልፅዋል፡፡

የተፈናቀሉትን ዜጎች ለመርዳትም የባንክ ሂሳብ መከፈቱን የነቀምቴ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ማሳወቁን የኦሮሚያ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በማህበራዊ ድህረገፁ አስፍሯል፡፡

በመሆኑም ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ አካላት በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ  ሂሳብ ቁጥር 937719

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  የሂሳብ ቁጥር 1000259030138

የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ  1000072131111 የሂሳብ ቁጥር መጠቀም ይቻላል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *