loading
እርስ በእርስ ከተዋደድንና ከተፋቀርን ኢትዮጵያ ለሁላችንም የምትበቃ ሀገር ናት አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

እርስ በእርስ ከተዋደድንና ከተፋቀርን ኢትዮጵያ ለሁላችንም የምትበቃ ሀገር ናት አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ ጋር ከቡኖ በደሌ ነዋሪዎች ጋር ዉይይት ባደረጉበት ወቅት ነዉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቡኖ በደሌ ነዋሪዎች እርስ በእርስ ከተዋደድንና ከተፋቀርን ኢትዮጵያ ለሁላችንም የምትበቃ ሀገር ናት ማለታቸዉን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ  ትላንት

ከመቱ ከተማ ነዋሪዎች ጋር የተወያዩ ሲሆን፤ በውይይቱም ነዋሪዎቹ የመንገድ፣የአውሮፕላን ማረፊያ እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታ ጥያቄዎች አቅርበዋል።

ነዋሪዎቹ ዩንቨርስቲ በከተማው መከፈቱን አድንቀው፤ ነገር ግን የአርሶ አደሩን ህይወት መለወጥ የሚችሉ የጥናት እና ምርምር ስራዎች እየተሰሩ አይደለም ብለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ሁላችንም አንድነታችን ማስጠበቅ ከቻልን የተነሱ ጥያቄዎች መመለስ የሚቻሉ ናቸው ማለታቸዉ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *