ኢ/ር ታከለ ኡማ እንደ አዲስ የተቋቋመውን የአዲስ አበባ ከፍተኛ ግብር ከፋዩች ቅርንጫፍ ፅ/ቤትን ጎበኙ፡፡
ኢ/ር ታከለ ኡማ እንደ አዲስ የተቋቋመውን የአዲስ አበባ ከፍተኛ ግብር ከፋዩች ቅርንጫፍ ፅ/ቤትን ጎበኙ፡፡
አዲስ የተቋቋመው የአዲስ አበባ ከፍተኛ ግብር ከፋይ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለ876 ግብር ከፋዮች ብቻ አገልግሎት እንዲሰጥ የተቋቋመ ሲሆን፤ የከተማዋ 60% ግብር የሚሰበሰብበት ቅርንጫፍ ነው፡፡
ይህ የከፍተኛ ግብር ከፋይ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከሌሎች መሠል ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በተሻለ መልኩ በሰው ሃይል እና በቴክኖሎጂ የተደራጀ ሲሆን ለሌሎች ግብር መሰብሰቢያ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶችም እንደ ልህቀት ማዕከልነት እንደሚያገለግልም ተጠቅሷል፡፡
ከግብር ከፋይ ነጋዴዎች ጋር በመሆን ማዕከሉን የጎበኙት ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ መሠል ማዕከላትን በቀጣይነት በዘመናዊ መልኩ በማደራጀት ለግብር ከፋዩ ምቹ የክፍያ ማዕከላትንም ይገነባል ማለታቸዉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡