ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሚሰማሩ 1 ሺህ ወጣቶች በዛሬው ዕለት ገለጻ አድርገዋል
የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከዛሬ ነሐሴ 1 ቀን እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2010 ዓ.ም የሚካሄድ ነው።
ዛሬ ይፋ በተደረገው የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ላይ ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 1 ሺ ተመራቂ ወጣቶች ተሳታፊዎች ናቸው።
ወጣቶቹ ከሚኖሩበት ክልል ባለፈ ወደ ሌሎች ክልሎች በመሄድ በተለያዩ ተግባራት ላይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ይሰጣሉ።
ይህ ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መካሄድ ሀገራዊ ስሜትንና የህዝብ ለህዝብ ማህበራዊ ትስስርን ያጎለብታል ተብሎ ይጠበቃል።