loading
ኢዜማ ያቀረበዉ የይግባኝ አቤቱታ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 22፣ 2013 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ኢዜማ ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ተቀበለ፡፡ ፍርድቤቱ አቤቱታዉን ተቀብሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ይዞ እንዲቀርብ ለሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ እንደሰጠዉ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ( ኢዜማ )
በማህበራዊ ገጹ አስታዉቋል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኢዜማ በ28 ምርጫ ወረዳዎች ምርጫው እንዲደገም ያቀረበው አቤቱታ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምላሽ እንዲሰጥ ውሳኔ አሳለፈ። ኢዜማ ቀደም ሲል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያስገባቸውን የቅሬታ ማስገቢያ ቅፆች ቅጂም ከሐምሌ 30 በፊት ቦርዱ ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ፓርቲው በማህበራ ገጹ አስፍሯል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *