loading
ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመች

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመች

የውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የመግባቢያ ሰነዱን  የተፈራረመው ገልፍ የኤሌክትሪክ ትስስር ከተባለ የባህረ ሰላጤው አባል ሀገራት  የኃይል አቀርቦት ተቋም እና የዓለም አቀፉ የኃይል ትስስር ድርጅት ጋር ነው፡፡

ሰነዱ የሃይል አቅርቦትን መሰረት ያደረገ ጥናት ለማካሄድ የሚያስችል  ነው ተብሏል፡፡

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይም  የውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የባህረ ሰላጤው የኤሌክትሪክ ትስስር ባለስልጣን ስራ አስፈፃሚ አህመድ አል ኢብራሂምና የዓለም አቀፉ የኃይል ትስስር ድርጅት ሊቀመንበር ሊዮ ዚኒያ ተገኝተዋል፡፡

በአትዮጵያና በባህረ ሰላጤው ሀገራት መካከል ወደፊት በሚኖረው የሃይል ትስስር የአዋጭነት ጥናት የሰነዱ አካል  እንደሆነ ከውሃ፣መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *