loading
ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ከሩስያ ጋር ተስመማች። 

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ከሩስያ ጋር ተስመማች።

የኒዉክለር ቴክኖሎጂን  ኢትዮጵያ  በህክምና፣ በግብርናና በኢንደስትሪ ዘርፍ ነዉ ትጠቀምበታለች የተባለዉ፡፡

በሩስያ በተካሄደው 11ኛው <<አቶምኤክስፖ>> ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ እና የሩስያ ስቴት አቶሚክ ኢነርጂ ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ጀነራል አሌክሲ ሌካቼቭ፤ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የትግበራ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በተለይ በአለም እያደገ የመጣውን የህምና ዘርፍ በኢትዮጵያ ለማዘመንና የቀዶ ጥገና ህክምናን የተቀላጠፈ ለማድረግ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ ለማዋል ሀገሪቱ እየሰራች መሆንዋን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ከኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  እንዳገኘነዉ መረጃ ኢትዮጵያ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችን ለመገንባት በዝናብ ላይ ጥገኛ ከሆነ የሃይል ማመንጫ ለመላቀቅ  ፊቷን   ወደ ድብልቅ ኢነርጂ አዞሯለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *