loading
ኢትዮጵያ ከታንዛኒያ 200 እስረኞችን ወደ ሃገር ቤት ለማስመለስ የበጀት እጥረት አጋጥሞኛል አለች

ኢትዮጵያ ከታንዛኒያ 200 እስረኞችን ወደ ሃገር ቤት ለማስመለስ የበጀት እጥረት አጋጥሞኛል አለች

አርትስ 26/02/2011

 

ኢትዮጵያ መንግሥት ከታንዛኒያ መንግሥት ጋር በመደራደር 96 ኢትዮጵያውያን እስረኞችን ወደ አገራቸው እንዲገቡ ማድረግ ቢቻልም፣ ቀሪዎቹን 200 እስረኞች ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ ግን እስካሁንአልተቻለም፡፡

እስረኞቹ በሞያሌ የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በኬንያና በታንዛኒያ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሉ የተያዙ ሲሆኑ  የታንዛኒያ መንግሥት እስረኞቹን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ቢሆንም፣ ወደ ኢትዮጵያየሚመለሱበትን የትራንስፖርት ወጪ የሚሸፍን ባለመገኘቱ በያሉባቸው እስር ቤቶች እንዲቆዩ ተደርጓል ነው የተባለው፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዜጎች ድጋፍና ክትትል ባለሙያው አቶ አስቻለው ከበደ ለሪፖርተር እንደገለፁት  ከዚህ ቀደም በነበረው አሠራር ያለውን የትራንስፖርት ወጪ የሚሸፍነው ዓለም አቀፍ የፍልሰትድርጅት (IOM) ነበር  ነገር ግን ድርጅቱ ለዚህ ዓመት የያዝኩት በጀት ጨርሻለሁ  በማለቱ የበጀት እጥረቱ ተከስቷል ፡፡

እንደ አቶ አስቻለው ገለጻ ጉዳዩ መፍትሔ ማግኘት ባለመቻሉ አቅም ያላቸውን የእስረኞች ቤተሰቦች በስልክ በማግኘት ትኬት ቆርጠው እንዲልኩ የማድረግ እንቅስቃሴ ለመጀመር ታስቧል፡፡

በሌላ በኩል የአብዛኞቹ  ወላጆች ትኬት የመግዛት አቅም እንደሌላቸው እና  በርካቶቹ አድራሻም ሆነ ተያዥ የሌላቸው ስለሆኑ፣ ቤተሰቦቻቸውን አፈላልጎ ማግኘት ከባድ እንደሆነባቸው የገለፁት ባለሞያውከ14 ዓመት ጀምሮ ያሉ ታዳጊዎች ከእስረኞቹ መካከል እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *