loading
ኢትዮጵያ በማር ምርት ያላትን ሃብት ያክል ተጠቃሚ አይደለችም ተባለ፡፡

በዓለም ባንክ የሚደገፈውና በኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚመራው የብሔራዊ የጥራት መሰረተ ልማት ፕሮጀክት በማር ምርት ጥራት ላይ ያተኮረ ውይይት ከማር ምርት አምራቾችና ባለድርሻ አካላት ጋር አድርጓል።
የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በፌስ ቡክ ገፁ እንዳሰፈረውበውይይቱ ኢትዮጵያ በማር ምርት ከቡና ባልተናነሰ የውጭ ምንዛሬ ገቢ የማግኘት አቅም ቢኖራትም የሚፈለገውን ያክል ገቢ እያገኘች አይደለም ተብሏል፡፡
የማር ምርት ጥራት ላይ የሚደባለቅበት ባዕድ ነገር ተጨምሮበት ምርቱ ከአለም ገበያ የመመለስ እክልም እየገጠመው መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጭ መላኩም ዘርፉን በእጅጉ ጎድቶታል ተብሏል፡፡
ዘርፉን ለማሳደግ የምርት ጥራት ላይ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባም በውይይቱ ተጠቁመዋል፡፡

አርትስ 24/12/2010

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *