loading
‹‹ኢትዮጵያ ለእኔ እኔም ለኢትዮጵያ›› የተሰኘዉ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ አርብ ስራ ይጀምራል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ለእኔ እኔም ለኢትዮጵያ›› የተሰኘዉ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ አርብ ስራ ይጀምራል፡፡

ተጠሪነቱ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆነው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ የፍታችን የካቲት 22 /2011ዓ.ም በይፋ ስራ ይጀምራል ተብሏል፡፡

ኤጀንሲው በሀገር ውጭ የሚኖሩ  ኢትዮጵያዊያን ለሀገራቸው የሚሰጡት እና ዲያስፖራዎች ከሀገራቸው የሚያገኙት የጋራ ጥቅም እና መብት ላይ ያተኮረው እንደሆነ ተነግሯል ፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት  በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ኤጀንሲው በውጭ የሚኖሩ ዜጎች መብት እና ጥቅም ለማስጠበቅ እና ዲያስፖራው በሀገሩ ጉዳዮች ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ‹‹ኢትዮጵያ ለእኔ እኔም ለኢትዮጵያ›› በሚል ዋና ሀሳብ የተቀቋቋመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ ውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ እኩል ተጠቃሚ እና ተደራሽ በሚያደርግ መንገድ የተቋቋመ መሆኑን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

ይህ ኤጀንሲ የውጭግንኙነት ባለሞያዎችን ጨምሮ በስሩ ወደ 53 ሰራተኞች እንዳሉት እና 60 በሚሆኑ ሚሲዮኖች እና በሀገር ውስጥ ክልሎች ቅርንጫፎች እንዳሉት ሰምተናል፡፡

ተቋሙ ወደስራ ሲገባ  በመጀመሪያ ከመረጃ ደህንነት ኤጀንሲ እና እንደ አለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት ካሉ አለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ ተቋማት ጋር በጋራ  በውጭ ሀገራት ስለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መረጃዎችን በማሰባሰብ ጠንካራ የመረጃ ቋት (ዳታ ቤዝ) የማዘጋጀት ስራ እንደሚሰራም ተነግሯል፡፡

በአጠቃላይ ሀገሪቱ ከዲያስፖራው ልታገኝ የምትችለውን ጥቅም ማስጠበቅ እና ዲያስፖራውም እንደዜጋ  ከሀገር ማግኘት ያለበትን ጥቅም  እና መብት በማስጠበቅ የሀገርንም የዲያስፖራውንም ተሳትፎ ለማገዝ የሚረዳ ነው ተብሏል፡፡

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *