loading
ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ግዜ የማር ወይንን አስተዋወቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2013 በኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ተቋም እና በጎንደር ዩኒቨርስቲ ትብብር ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረተ አዲስ የማር ወይን የቅምሻ እና የማስተዋወቂያ ሥነ ሥርዓት ትናንት ማምሻውን በስካይ ላይት ሆቴል ተካሄዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ ጥናታዊ ትንታኔ፣ ውይይት፣ ማብራሪያ፣ ምሥጋና፣ ወደ ፊት የታሰቡ ዕቅዶች እና የግብይት መሥመሩን መቀላቀያ ሐሳብ ቀርበውበታል። የጥናቱ ባለቤት ፕሮፌሰር ብርሃኑ አንዷለም እንደገለፁት ይህ የማር ወይን ከማር ከውሃና ከጌሾ የተሠራ ሲሆን በዋናነት በግብይቱ ጌሾን በመመሥረት የራሳችንን መታያ ቀለም ይዘን ለመምጣት ነው ብለዋል።

አክለውም ጥናታቸው ከሦስት ዓመት በላይ የፈጀ መሆኑን ገልፀው  ኢትዮጵያ ውስጥ በእናቶችና በሌሎች ባለሙያዎች የሚታወቀው የአልኮል ማብላያ በይዞታው ባሕላዊ በመሆኑ ወደ ኢንዱስትሪ ከፍ ማለት አልቻለም፤ ሥለዚህ  ይህ የማር ወይን የተሻለ አድርጎ ለማዘመን አመላካች መሆኑን
ተናግረዋል። ይህን የማር ወይን ለውጭ ገበያ በማቅረብ እና የሥራ ዕድል በመፍጠር የአገራችንን ኢኮኖሚ ከፍ በማድረግ እንዲሁም የውጭ ምንዛሬን በመቀነስ ረገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊያደርግ እንደሚችል በጥናቱ ጥቅም አመላክተዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *