loading
ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች በቦ ክላሲክ ውድድር አሸናፊ ሆኑ

ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች ታምራት ቶላ እና ነፃነት ጉደታ የቦ ክላሲክ ውድድር አሸነፉ፡፡

 

ውድድሩ በጣሊያን ቦልዛኖ ከተማ በየዓመቱ የሚከናወን ሲሆን በወንዶች 10 ኪ.ሜ እና በሴቶች 5 ኪ.ሜ የሚካሄድ የጎዳና ላይ ሩጫ ነው፡፡

 

ለ43ኛ ጊዜ በተካሄደ ውድድር በወንዶች ኢትዮጵያዊው አትሌት ታምራት ቶላ 10 ኪሎ ሜትሩን በ 28 ደቂቃ ከ 12 ሰከንድ በሆነ ጊዜ መጨረስ ችሏል፡፡ ኬንያዊው ቢሪች ጃይሩስ በ28 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ሁለተኛ፣ ዩጋንዳዊው ቼሊሞ ኦስካር በ28 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ሶስተኛ ወጥቷል፡፡ የ42ኛው ቦ ክላሲክ ውድድር ባለክብር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሙክታር እድሪስ አራተኛ ደረጃ ወጥቷል፡፡

 

በሴቶች 5 ኪ.ሜ አትሌት ነፃነት ጉደታ ውድድሩን በ15 ደቂቃ ከ 46 ሰከንድ በአንደኝነት ስትፈፅም ኬንያዊቷ አትሌት ኪሳ ጃኔት በ15፡ 49 ሁለተኛ፣ ማዙሮናክ ቮልሃ ከቤሎ ሩሲያ በ16፡ 08 ሶስተኛ ደረጃ ይዘው ጨርሰዋል፡፡ ነፃነት ጉደታ የ2016 ውድድርን በበላይነት ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡

 

ቦ ክላሲክ ከ1975 ጀምሮ መካሄድ የጀመረ ሲሆን ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተለይ በወንዶች በተደጋጋሚ ባለድል ይሆኑበታል፡፡

 

በውድድሩም በተመረጡ አዋቂ አትሌቶች መካከል ዘወትር በአዲስ ዓመት ዋዜማ ሲካሄድ ከ10 ሺ በላይ ተመልካቾች ይታደሙበታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *