loading
ኢትዮጵያን የመከላከያ ሰራዊቷንና አየር መንገዷን ለማዘመን ከፈረንሳይ ጋር ስምምነት ፈረመች

ኢትዮጵያን የመከላከያ ሰራዊቷንና አየር መንገዷን ለማዘመን ከፈረንሳይ ጋር ስምምነት ፈረመች

ርትስ 20/02/2011

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትንና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለማዘመን ከፈረንሳይ መንግስት ጋር ስምምነት ተፈረመ። ፈረንሳይ ለአየር መንገዱ ከ100 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ወጪ ታደርጋለች ተብሏል።

ስምምነቱ የተፈረመው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በፈረንሳይ ፓሪስ ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ትላንት ከተወያዩ በኋላ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የፈረንሳይ መንግስትን አምነውናሀገራችን ብለው ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የተሰጠው ፍቅር ወደፊትም እንዳይቀዘቅዝ ፣ ኑሯቸውም ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል ፕሬዝዳንት ማክሮንን መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡

ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የመጀመሪያ የሆነውን የአውሮፓ ጉብኝት በፓሪስ የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በዛሬው ዕለት ወደ ጀርመን በመጓዝ ከመራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋርተገናኝተዋል፡፡

ቁጥራቸው ከ25 ሺህ የማያንሱ ኢትዮጵያውያን ከቀናት በኋላ ወደ ፍራንክፈርት በመጓዝና በመሰባሰብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ያነጋግራሉ ተብሎ ቀጠሮ መያዙም ተሰምቷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *