loading
አፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ ማግኘት እንሚገባው ኬኒያ አሳሰበች::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1፣ 2013 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋረ ከኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሪይቸል ኦማሞ ጋር በሁለትዮሽ እና በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ በጽሕፈት ቤታቸው ውይይት አድርገዋል። አምባሳደር ሬድዋን በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ፣ በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር እንዲሁም የትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለአምባሳደሯ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

6ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐሃዊና ተዓማኒ እንዲሆን ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ሆኖ እንዲደራጅ ከማድረግ ጀምሮ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡በግድቡ ድርድር ዙሪያ በኢትዮጵያ በኩል በመጀመሪያ የግድቡ የውኃ ሙሌት በተመለከተ ስምምነት ላይ በመድረስ ሌሎች የውኃ ስምምነቶች ግን የሌሎችንም የተፋሰሱ ሀገራት ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ ቀጥሎ መታየት እንደሚገባው በኢትዮጵያ በኩል የተያዘ አቋም መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

አሁን በአፍሪካ ሕብረት በኩል ድርድሩን በየደረጃው በመክፈል ለማካሄድ የቀረበው ሐሳብ ከኢትዮጵያ አቋም ጋር የሚስማማ ስለመሆኑ ገልጸዋል ሚስትር ዴኤታው። የትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተም አስፈላጊው የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት በዋናነት በመንግሥት በኩል እየቀረበ መሆኑ አብራርተዋል፡፡
መላክተዋል።

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሪይቸል ኦማሞ ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ መርህ መሰረት ጉዳዮች እልባት ማግኘት እንዳለበት ሀገራቸው የምታምን መሆኗን ገልጸዋል። ሚኒስትሯ ኢትዮጵያና ኬኒያ ባላቸው ዘመናት ያስቆጠረ ግንኙነት የተፈራረሟቸውን በርካታ ስምምነቶች ተግባራዊነት በማፋጠን ግንኙነታቸውን የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈለግም ጠቅሰዋል፡፡ መረጃውን ያገኝነው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *