loading
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኳታር መንግስት ለኢትዮጵያ የሕክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረጉ አመሰገኑ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኳታር መንግስት ለኢትዮጵያ የሕክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረጉ አመሰገኑ::

“የኳታር መንግሥት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች፣ የሕክምና ጓንቶች፣ ፊትን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍኑ እና ሰውነትን ከንክኪ የሚከላከሉ ልብሶች እንዲሁም ሌሎች ኮቪድ-19ን የመከላከያ ግብአቶች መላካችሁ  ወረርሽኙን ለመግታት የምናደርገውን ጥረት ይደግፋል ነዉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ድጋፉ 470 ሺ ማስክ ፣ 70 ሺ ኤን 95 ማስክ ፣ 60 ሺ ጓንት ፣ 12 ሺ 5 መቶ የፊት መከላከያና 5ሺ 700 የህክምና ባለሙያዎች ሙሉ የሰዉነት መሸፈኛ ቁሶች ናቸዉ፡፡

ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በመገኘት ድጋፉን የተቀበሉት የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዩ የኳታር መንግስት ፤ላቀረብነዉ ጥያቄ  ፈጣን ምላሽ በመስጠት በመተባበሩ እጅግ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል፡፡የጤና ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ በበኩላቸው ኢትዮጵያና ኳታር በጤናው ዘርፍ ያላቸው ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን አንስተዋል።    ”ኳታር ለኢትዮጵያ ድጋፍ ስታደርግ ይህ የመጀመሪያው አይደለም” ያሉት ሚኒስትር ደኤታው በኳታር መንግስት ድጋፍ እየተገነባ ያለው የኩላሊት ህክምና ማዕከል እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል።በተለይ የህክምና ባለሙያዎች ራሳቸውን የሚጠብቁበት መከላከያ ቁሳቁስ የሚያስፈልጋቸው ወሳኝ ወቅት እንደመሆኑ ድጋፉ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን አመልክተዋል።  በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር ሀማድ ሞሀመድ አልዶሳሪ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያና ኳታር ጥሩ የሚባል ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸዉ ድጋፋቸዉን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡”ዛሬ ያደረግነው ድጋፍ ኢትዮጵያ በሽታውን ለመከላከል የጀመረችውን ጉዞ እንደሚያጠናክር ትልቅ እምነት አለን” ብለዋል። አገራቸው ለኢትዮጵያ የምተሰጠውን ድጋፍ እንደምትገፋበትም አምባሳደሩ አረጋግጠዋል።

 

 

 

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *