loading
አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን ጨምሮ በአራት ክልሎች የዕጩዎች ምዝገባ ዛሬ ይጀመራል::

አዲስ አበባ፣የካቲት 8፣ 2013 አዲስ አበባ እና ድሬዳዋን ጨምሮ በአራት ክልሎች የዕጩዎች ምዝገባ ዛሬ ይጀመራል:: አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ኦሮሚያ እና ሐረሪ ክልሎች የዕጩዎች ምዝገባ ዛሬ ይጀመራል። ምዝገባው የሚከናወነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዕጩዎች ምዝገባ ባወጣው ከየካቲት 08 እስከ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ነው።

የምርጫ ክልሎቹ በተጠቀሱት ጊዜያት የዕጩዎች ምዝገባ የሚያከናውኑት ለምርጫ ክልል እና ለዞን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሊያገለግሉ የሚችሉ ቢሮዎችን በማዘጋጀታቸው መሆኑን ቦርዱ ገልጿል። በአፋር፣ አማራ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ እና ሶማሌ ክልሎች ከየካቲት 05 እስከ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ለዕጩዎች ምዝገባ የሚውሉ ቁሳቁሶች እንደሚጓጓዙ እና የዕጩዎች ምዝገባ አስፈጻሚዎች ሥልጠና እንደሚሰጥም ቦርዱ አመልክቷል። ከየካቲት 15 እስከ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ደግሞ የዕጩዎች ምዝገባ እንደሚከናወን ቦርዱ ባለፈው ሳምንት መወሰኑ ይታወሳል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *