loading
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2012 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ ጀመሩ ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2012 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ ጀመሩ :: በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ትምህርቱን እንዲከታተሉ እና ከአማካሪዎቻቸው ጋርም የሚገናኙበት ምቹ ሁኔታ በመኖሩ ትምህርታቸውን ማጠናቀቅ ጀምረዋል።በሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ኤባ ሚጀና፣ የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ባይኖርም ጅማ እና ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ መጀመራቸውን ጠቅሰዋል።ሆኖም ግን ትምህርታቸውን የማይጨርሱ ተማሪዎች እንደሚኖሩም ጠቁመዋል።ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ለመጨረስ የቻሉት በተመቻቸው የቴክኖሎጂ የማስተማሪያ ዘዴ በአግባቡ መጠቀም በመቻላቸው እንዲሁም በተማሪው እና በአማካሪዎቻቸው ጥንካሬ እንደሆነ የጠቆሙት ዶ/ር ኤባ፣ የትምህርት ተቋማቱም በየጊዜው አስፈላጊውን ክትትል እና ግምገማ በማድረግ ውጤታማ መሆኑ መቻላቸውን አመልክተዋል።

የመጨረሻ ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን በወረርሽኙ ምክንያት ባለመማራቸው፣ አንዳንዶችም የመጀመሪያ መንፈቅ ፈተና ባለመፈተናቸው በዚህ ክረምት ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች አይኖሩም ብለዋል-ዶ/ር ኤባ።ሆኖም የተማሪዎቹን ቀጣይ ሁኔታ በተመለከተ ወረርሽኙ ቢቆም መደረግ ስላለበት ሁኔታ በየሳምንቱ ከየትምህርት ተቋማቱ የትምህርት አመራሮች ጋር ግምገማ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።በወረርሽኙ ምክንያት ትምህርት እንዲቋረጥ ሲደረግ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸው በቤታቸው የሚያነብቡአቸው የትምህርት ሰነዶች እንዲሰጣቸው የሚል አቅጣጫ ተሰጥቶ እንደነበርም አመልክተዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *