loading
አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሸይክ ሞሐመድ በቅርብ ጊዜ የፀጥታ ስራውን ከሰላም አስከባሪ ሃይሉ እንረከባለን አሉ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2014 አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሸይክ ሞሐመድ በቅርብ ጊዜ የፀጥታ ስራውን ከሰላም አስከባሪ ሃይሉ እንረከባለን አሉ፡፡
በሀገሪቱ የደህንነት ስጋት የሆነውን አልሸባብን ለማጥፋት ቁጥር አንድ መፍትሄ ወታደራዊ ጥንካሬ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሃይል እስካሁን ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡


ፕሬዚዳንቱ ከአናዶሉ የዜና ወኪል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የሀገራቸው ቀዳሚ ችግሯ የፀጥታ ጉዳይ መሆኑን በመግለጽ ይህን ምስቅልቅል መልክ ለማስያዝ ተግተው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡ በመሆኑም በሁለት ወራት ውስጥ በራሳችን አቅም የፀጥታውን ስራ ሙሉ በሙሉ በመረከብ ሀገራችንን ራሳችን እንጠብቃታለን ብለዋል፡፡
በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት የቢሮ ቆይታቸው ህዝቡን ወደ አንድነት የሚያመጣ ስራ በመስራት በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተራራቁ ቡድኖችን የሚያቀራርብ ድልድይ ማበጀት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡


ህዝቡ በሀገሩ ጉዳይ ጊዜና ቦታ ሳይገድበው ሀሳቡን በነፃነት መግለፅ እንዲችልና ጠቃሚ ውይይቶችን እንዲያደርግ የፖለቲካውን ሜዳ ማስፋትም ዋነኛ ስራቸው እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ በሃሳብ ከሚሞግቷቸው ተቃዋሚዎች ጋር መደማመጥን መርህ አድርገው በጋራ በመስራት ሶማሊያን ዳግም ለመገንባት እንደሚጥሩም አብራርተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *