loading
አስተዳደሩ ተበታትነው የነበሩ ተቋማትን ወደአንድ ማዕከል ላሰባስብ ነው አለ

አስተዳደሩ ተበታትነው የነበሩ ተቋማትን ወደአንድ ማዕከል ላሰባስብ ነው አለ

አርትስ 16/02/2011

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተበታትነው የነበሩ የተለያዩ ተቋማት ከመጪው ሰኞ ጀምሮ አገልግሎታቸውን በአንድ ማዕከል መስጠት ይጀምራሉ ።

የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ፣የመሰረተ ልማት ቅንጅት እና የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን፣የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ፅህፈት ቤት እንዲሁም ፕላን ኮሚሽን ቀድሞ በተለያየ አካባቢ እና በተበታተነ መልኩ አገልግሎታቸውን ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡

ይህም ነዋሪው እና ተገልጋዩን ለእንግልት ሲዳርግ ቆይቷል ። በመሆኑም የነዋሪውን ተደጋጋሚ ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት እነዚህን ተቋማት ተገልጋዪችን ለማስተናገድ ምቹ በሆነ ቦታ በአንድ ማአከል በማሰባሰብ ለነዋሪው ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል፡፡

ከዚህ ቀደም ይሰጥ የነበረው አገልግሎት ተገልጋዩን ለከፍተኛ ወጪና እንግልት በመዳረጉ፤ ተደጋጋሚም ቅሬታ ከአገልግሎት ፈላጊው ቀርቧል ተብሏል።

በተለይም የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮና ተበታትነውና ተለያይተው ያሉ ተጠሪ ተቋማቱ ወደ ማዕከል መምጣታቸው ለነዋሪው የሚሰጠው አገልግሎት ምቹ፣ወጪና ጊዜ ቆጣቢ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *