loading
አርሷደሯ ጌሪ አሜሪካ ተብሎ ለሚጠራው የእህል ፈጅ ትል መድሀኒት አገኙ፡፡

አርሷደሯ ወ/ሮ ታቦቴ አባተ በቦኖ በደሌ ዞን አርሶ አደር ናቸው። ከችግራቸው በመነሳትም ጌሪ አሜሪካ ለተባለ ትል አዲስ የትል ማጥፊያ ፈጥረዋል።
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ሴንተር በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ ጌሪ አሜሪካ በቆሎን በብዛት የሚያጠቃ ትል ነው።ትሉ ቁጥጥር ካልተደረገበት በበቆሎ ምርት ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሳል። በአንድ ሌሊት በ1500 እጥፍ ሊራባ ይችላል።
ወ/ሮ ታቦቴ ታዲያ ይህን ትል የሚገድል መድሀኒት በአካባቢያቸው ካሉ ግብዓቶች አግኝተዋል።
ወ/ሮ ታቦቴ ሎሚ አሲድ እንደሆነ በማሰብ አጓትም አሲድነት አለው ብለዉ በማመን በአንድ ላይ በመበጥበጥ ትሉ ላይ በመርጨት ይሞክሩታል። የተሰራዉን ማጥፊያ ትሉን ያለበትን ቦታ እየለዩ አንድ በአንድ ይረጩታል። ውጤቱም ጥሩ ሆንዋል።
ይህ መደኃኒት ትሉን በቶሎ የመግደል አቅም እንዳለው ባለሙያዎች አረጋግጠዋል።
መደኃኒቱ ከሳይንሳዊ መድኃኒት ይልቅ ተመራጭ የሚያደርገውም አርሶ አደሮች በቀላሉ የሚያዘጋጁትና ተፈጥሯዊ ስለሆነ መርዝንት ስለሌለዉ ነዉ ተብሏል፡፡
ወ/ሮዋ ለወደፊት ሌላ መድኃኒት የመፍጠር ሐሳብ እንዳላቸው የተናገሩ ሲሆን፤ የነቀዝ መድኃኒት የመስራት ፍላጎት አለኝም ሲሉ ተደምጠዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *