አምራችና ጤናማ ማህበረሰብ ለማፍራት መሰራት እንዳለበት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሰተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ተናገሩ፡፡
ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የኦሮሚያ ጤና ኮንፍረንስ ላይ ነው፡፡ በመንግስት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እንዳሉ ሆነው በባለድርሻ አካላትና ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላት ከፍተኛ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ረ ደረጀ ዱጉማ በበኩላቸው የቢሮውን የ2010 የስራ አፈፃፀምና የ2011 ዕቅድን ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡
አሁን በክልሉ አገልግሎት እየሰጡ ካሉ 91 ሆስፒታሎች በተጨማሪ በቀጣይ 12 አዳዲስ ሆስፒታሎች ወደ ስራ እንደሚገቡ አሳውቀዋል፡፡