loading
አሜሪካ በ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ለቱርክ ልትሸጥ ነው

አሜሪካ በ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ለቱርክ ልትሸጥ ነው

አርትስ/11/04/2011

ለቱርክ  በ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ  እንደሚከናወን ይፋ ያደረገው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ነው፡፡

ሮይተርስ የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጠቅሶ እንደዘገበው የቱርክን የመከላካያ አቅም በማጠናከር በአካባቢው የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ  እንደሚያስችላት ታምኖ ነው የመሳሪያ ሽያጩ የሚካሄደው።

በዚህም 80 የተሻሻሉ ፓትሪዮት ኤም አይ ኤም-104ኢ ሚሳኤሎችን ጨምሮ 60 የተለያዩ

የጦር መሳሪያዎች ለቱርክ ይሸጣሉ ተብሏል።

ዘመናዊ የራዳር  መሳሪያዎች፣ የጠላት ወታደሮች እንቅስቃሴ መቆጣጠሪያ እና የመገናኛ መሳሪያዎች ለሽያጭ ቀርበዋል ።

ቱርክ ከዚህ በፊት ከአሜሪካ የጦር መሳሪያዎችን ለመግዛት ጥረት ብታደርግም አሜሪካ  ለሽያጩ  ፈቃደኛ ባለመሆኗ  ቱርክ በቅርቡ ከሩሲያ ጋር ለጦር መሳሪያ ግዥ ከስምምነት መድረሷ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎ  አሜሪካ የቱርክ እና ሩሲያ ስምምነት አላማረኝም  ስትል ቆይታለች፡፡

በመሆኑም አሜሪካ አሁን ከቱርክ ጋር ያደረገችው የጦር መሳሪያ ሽያጭ ግንኙነት  ቱርክ ከሩሲያ ጋር እያደረገች ያለውን ተመሳሳይ  ስምምነት ለመፎካከር እንደሆነ  ተጠርጥሯል፡፡ ሮይተርስ እንዳስነበበው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *