loading
አሜሪካ በአንድ ሳምንት አንድ ሚሊዮን ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 07፣ 2013 አሜሪካ በአንድ ሳምንት አንድ ሚሊዮን ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተሰማ:: የኮሮናቫይረስ ስርጭት እንደአዲስ የተባባሰባት አሜሪካ በየቀኑ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው እንደሚያዙ እየተነገረ ይገኛል፡፡ በዚህም የተነሳ አሁን ላይ በሀገሪቱ በኮቪድ-19 ወረርሽ የተያዙ ሰዎች ከ11 ሚሊዮን በላይ መድረሱ ነው የተነገረው፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው አሜሪካ በተለያዩ ግዛቶች አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን የመዝጋት እርምጃዎችን ለመወሰድ ተገዳለች፡፡ ለአብነትም የዋሽንግተን ግዛት ምግብ ቤቶች ደንበኞቻቸውን በሬስቶራንታቸው ውስጥ እንዳያስተናግዱ እገዳ ጥላለች፡፡ ኦሬጎን እና ኒው ሜክሲኮም የቫይረሱ ስርጭት ከፍ ማለቱን ተከትሎ ከቅዳሜ ጀምረው ጥብቅ የሆነ የእቅስቃሴ እቀባ ደንግገዋል፡፡

በሀገሪቱ በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ246 ሺህ በላይ የደረሰ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየቀኑ በአማካይ ከ900 በላይ ሰዎች እንደሚሞቱም ተነግሯል፡፡ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆች ዓመት መገባደጃ የኮቪ-19 ክትባትን ለህዝቡ መስጠት እንደሚጀምሩ መናገራቸው ይታወቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *