loading
አልበሽር በምእራባዊያን ማእቀብ መማረራቸውን ተናገሩ

አርትስ 17/04/11

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር አሜሪካ የጣለችባች ማእቀብ ሙሉ በሙሉ አለመነሳቱ የሱዳንን ኢኮኖሚ በእጂጉ እንደጎዳው ተናግረዋል፡፡

አልበሽር ሀገራቸው በዋጋ ንረት ሳቢያ በተቃውሞ ሰልፍ እየታመሰች ባለችበት ወቅት ይህን ማለታቸው  ችግሩን ለማተባበል ያደረጉት አስመስሎባቸዋል፡፡

“አሁን ያለብንን ኢኮኖሚያዊ ችግር ለመወጣት በምንታገልበት ወቅት የሱዳንን እድገት የማይፈልጉ ወገኖች ምክንያት ፈልገው አለመረጋጋት እንዲፈጠር ይጥራሉ”  ሲሉም ወደ ሌሎች ጣታቸውን ጠቁመዋል ነው የተባለው፡፡

በአሁኑ ወቅት በካርቱምና በሌሎችም ከተሞች “ኑሮ ከበደን ዋጋ ያለ አግባብ ተጫነብን” የሚሉ ሱዳናዊያን ለተቃውሞ ሰልፍ ጎዳና ወጥተው ነው የሰነበቱት፡፡

በሀገሪቱ በተቀሰቀሰው አመፅ ሳቢያ 37 ሰዎች በፖሊስ ሀይሎች መገደላቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም በሪፖርቱ ገልጿል፡፡

ሱዳንን ማስተዳደር ከጀመሩ 39 ዓመታትን ያስቆጠሩት አልበሽር ተቃውሞው ፋታ ሲነሳቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለማድረግ ቃል ቢገቡም ሀገሪቱ ያለባት ችግር ያን ለማድረግ እንደማይፈቅድላት የሚያመላክት ንግግር ነው ያደረጉት፡፡

ከማእቀብ በተጨማሪ የሱዳንን ኢኮኖሚ ያዳከመው ደቡብ ሱዳን ከተገነጠለች በኋላ የነዳጅ  ምርት ድርሻዋ በመቀነሱ መሆኑ ይነገራል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *