loading
አልበሽር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ወደ ግብፅ ያቀናሉ

አልበሽር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ወደ ግብፅ ያቀናሉ

አርትስ 27/02/2011

 

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኡመር ሃሰን አልበሽር በዛሬው ዕለት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ግብፅ እንደሚያቀኑ ተነገረ።

በግብፅ የሱዳን አምባሳዳር አብዱል ሃሊምን ጠቅሶ ሱዳን ትሪቡዪን እንዳስነበበው  አልበሽር ወደግብጽ የሚያመሩት በፕሬዚዳንት አልሲሲ በተደረገላቸው ግብዣ መሰረት ነው።

አልበሽር በግብጽ ቆይታቸው ለሁለተኛ ጊዜ በሻርም አልሼክ ከተማ እየተካሄደ ባለው  የዓለም ወጣቶች ፎረም ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በካርቱም ተካሂዶ በነበረው የሱዳንና ግብፅ ከፍተኛ ኮሚቴ አባላት ውይይት ውጤት ላይ ከፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ ጋር ይወያያሉ ተብሏል።

የሱዳንና ግብፅ ከፍተኛ ኮሚቴ ውይይት መጨረሻ ላይ ሃገራቱ በ12 የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በቅርቡ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እየተሻሻለ መምጣቱ ቢነገርም፥ ኢትዮጵያ በምትገነባው የህዳሴ ግድብ ጉዳይና በሀገራቱ ድንበር አካባቢ ላይ ያለው ግጭት ግን ልዩነታቸውን እንዳያሰፋው ተሰግቷል ብሏል ዘገባው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *