loading
አለም አቀፍ የካንሰር ቀን በሀገራችን ለ12ኛ ጊዜ ተከበረ

አለም አቀፍ የካንሰር ቀን በሀገራችን ለ12ኛ ጊዜ ተከበረ

የዘንድሮው አለም አቀፍ የካንሰር ቀን ‹‹እራሴን እና ቤተሰቤን ከካንሰር ለመከላከል ቆርጫለሁ›› በሚል መሪቃል ነው ተከብሮ የዋለው፡፡

በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የካንሰር አማካሪ ዶክተር ኩኑዝ አቡበከር ለአርትስ እንደተናገሩት ቀኑን አስቦ መዋል ያስፈለገው ማህበረሰቡ ውስጥ ካንሰር የማይድን በሽታ ነው ለሚለው አመለካከት ግንዛቤን ለመፍጠር ነው፡፡

እንደ ዶክተር ኩኑዝ ገለፃ ካንሰር በጊዜ ከተደረሰበት መከላከል እና ማዳን የሚቻል ህመም ነው፡፡

በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ65ሺህ በላይ አዳዲስ የካንሰር ህሙማን የሚመዘገቡ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 30 በመቶ የሚሆኑት የጡት ካንሰር የተያዙ ሰዎች ናቸው፡፡

የመሃጸን በር እና የአንጀት ካንሰር ደግሞ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በሀገራችን በብዛት የሚስተዋሉት የካንሰር አይነቶች ናቸው፡፡

ከካንሰር ህክምና ጋር ተያይዞ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን በገፃቸው እንዳሰፈሩት ሰባት የጨረር ህክምና መሳሪያ (LINAC Machine) በ26.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ግዥ ተፈፅሞ ሶስቱ በተከላ ላይ ሲሆን አራቱ ደግሞ የማዕከሉ ግንባታ እስኪጠናቀቅ እየጠበቁ ይገኛል ፡፡
ከሀገራችን የካንሰር ህመም አይነት ጋር ጥናት ተደርጎ 51 አይነት የኬሞቴራፒ መድኀኒቶች ግዥ ተፈፅሞ ከመድኀኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ቀጥታ ወደ ካንሰር ማእከላት የሚሄድበት አሰራርም መዘርጋቱን ሚኒስትሩ በገፃቸው አስፍረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *