loading
ናይጄሪያዊው መንገደኛ ህገወጥ ገንዘብ ይዞ ከሀገር ሊወጣ ሲል ተያዘ

ናይጄሪያዊው መንገደኛ ህገወጥ ገንዘብ ይዞ ከሀገር ሊወጣ ሲል ተያዘ

አርትስ 21/04/2011

 ተጠርጣሪ ኢፋኒቸኩ አማኑኤል ኢኬዲቡ የተባለ ናይጀሪያዊ መንገደኛ፤ ህገወጥ 141ሺህ ዶላር ይዞ በቦሌ ኤርፖርት በኩል አድርጎ ወደ ናይጀሪያ ሊወጣ ሲል ታኅሣሥ 20/2011 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር መዋሉን በገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ ኮሚሽን የቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ናይጀሪያዊው መንገደኛ ህገወጥ ገንዘቡን ይዞ ሲንቀሳቀስ በኤክስሬይ የፍተሻ ማሽን አማካኝነት፣ በጉምሩክ ሠራተኞች እና በብሔራዊ መረጃ ደኅንነት ባለሙያዎች ከፍተኛ አስተዋጾ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩ ተይዟል፡፡

ቅ/ፅ/ቤቱ እያደረገ ያለው ክትትል እና ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያሳወቀ ሲሆን በቀጣይ ህብረተሰቡ ህገወጦችን በንቃት በመከታተል ለህግ እንዲያቀርቡ በማድረግ የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *