loading
ቻድና እስራኤል ከዘመናት በኃላ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ጀመሩ

አርትስ 17/03/2011

የቻዱ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ዴቢ ታሪካዊ የተባለውን ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ኢየሩሳሌም አቅንተዋል፡፡

የእስራኤሉ ጋዜጣ ዘ ጀሩሳሌም ፖስት እንደዘገበው ቻድና እስራኤል ላለፉት 46 ዓመታት ምንም ዓይነት የዲሎማሲ ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡

እናም የአሁኑ የዴቢ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ለሚኖረው የዲፕሎማሲ ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል ተብሎለታል፡፡

እስራኤል እንደአገር ከተመሰረተች አንስቶ በሁለቱ ሀገራት መካከል ይሄ ነው የሚባል ግንኙነት አልነበራቸውም ፤ አዲሱ ወዳጅነት በጠቅላይ ሞኒስትር ቤናሚን ኔታናያሁ ጥረት የመጣ ነው ያለው ደግሞ ሚድል ኢስት ሞኒር ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ዴቢና ኔታናያሁ በሚያደርጉት የጋራ ቆይታ በፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው ውይይታቸውን ያካሂዳሉ ተብሏል

ባለፈው ዓመት የኔታናያሁ አስተዳደር ቻድ በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል የተነሱባትን ተቃዋሚዎች ትወጋበት ዘንድ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንዳደረገላት ሮይተርስ በዘገባው አስነብቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *