loading
ቻይና እና አሜሪካ በጂቡቲ ወደብ ተፋጠዋል

አርትስ 05/04/2011

የአሜሪካ ታዋቂ ሴናተሮች ቻይና የጂቡቲን የወደብ ተርሚናል ከተቆጣጠረች በምስራቅ አፍሪካ የሚኖራት ተፅእኖ ቀላል እንደማይሆን አስጠንቅቀዋል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው ጂቡቲ ከተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ጋር የነበራትን  የዶራሌ እቃ ማራገፊያ ወደቧን የማስተዳደር  ኮንትራት ማቋረጧ  የነገሩን አቅጣጫ ሊቀይረው ይችላል፡

የሴናተሮቹ ስጋት የሚነጨው ጂቡቲ ከቻይና ባለባት ትልቅ ብድር ሳቢያ ተርሚናሉ የቻይና መንግስት ንብረት በሆነ  ኩባንያ እንዲተደዳር ልትፈቅድ ትችላለች ከሚል መነሻ ነው፡፡

የሪፓብሊካኑ ሴናተር ማርኮ ሮቢዮ እና የዴሞክራቱ ተወካይ ሴናተር ክሪስ ማቲስ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ በፃፉት ደብዳቤ ነው ይህን ጉዳይ ሀገራቸወ እንድታስብበት ያሳሰቡት፡፡

የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባሎቹ  ቻይና ለአሜሪካ የኢኮኖሚና የደህንነት ስጋት እየሆነች መምጣቷ ቸል የሚባል ጉዳይ መሆን የለበትም ብለዋል፡፡

ዘገባወች እንደሚያመላክቱት ቻይና ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ ብድር ከሰጠች በኋላ የመመለሻ ጊዜው ሲያልቅ ቋሚ ንብረቶችን በመውረስ የራሷ አድርጋለች፡፡

በዚህም የተነሳ ኬንያን ጨምሮ አንዳንድ ሀገሮች ከቻይና የሚቀርብላቸውን የብድር እንስጣችሁ ጥያቄ አንፈልግም ማለት ጀምረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *