loading
ትራምፕ ወደአሜሪካ ገዳይ አስገብተዋል ብለው ዴሞክራቶችን እያብጠለጠሉ ነው

አርትስ 23/02/2011

 

አንድ ሜክሲኳዊ የአሜሪካ ፖሊስ መኮንኖችን ገደልኩ ብሎ የለቀቀውን ተንቀሳቃሽ ምስል በትዊተር ገጻቸው ያጋሩት ዶናልድ ትራምፕ ግለሰቡን ወደአሜሪካ ያስገቡት ዴሞክራቶች ስለሆኑ ለድርጊቱ ሃላፊነት መውሰድ አለባቸው እያሉ ነው።

ቪዲዮው ከአሜሪካ ሁለት ጊዜ የተባረረው ሉዊስ ባካሞንቴስ የተባለ ሜክሲካዊ ካሊፎርኒያ ውስጥ ሁለት ፖሊሶችን መግደሉን እየሳቀ ሲናገር የሚያሳይ ነው ተብሏል። ከዚህም በላይ በገደልኩ ደስ ይለኝ ነበር ብሏል ሉዊስ በቪዲዮው ላይ።

ቪዮውን ማን እንዳዘጋጀው ባይታወቅም ፕሬዚዳንት ትራምፕ በትዊተር እና ኢንስታግራም ማህበራዊ ገጻቸው ላይ  “ህገወጡ ስደተኛ ሉዊስ ባካሞንቴስ ዜጎቻችንን ገድሏል። ወደዚህ ሃገር አስገብተው እንዲቀመጥ ያደረጉት ደግሞ ዴሞክራቶች ናቸው” የሚል የጽሁፍ መግለጫ አክለው ለተከታዮቻቸው አጋርተውታል።

በቪዲዮው ላይ ትራምፕ  “ዴሞክራቶች በሃገራችን ላይ የሚያካሂዱት ነገር ሁሉ ያስቆጣል።ፐብሊካንን አሁን ምረጡ።”  የሚል ጽሁፍ ማከላቸው ድርጊቱን ለምርጫ ቅስቀሳ እየተጠቀሙበት ነው አስብሎ አስተችቷቸዋል።

ትራምፕ ይህን ያልተረጋገጠ ቪዲዮ እውነት እንደሆነ አድርገው በማህበራዊ ሚዲያዎች ማጋራታቸው በታሪክ መጽሃፍ የሚኮነን ትልቅ ስህተት ነው ብለዋቸዋል ተቺዎቻቸው።

ትራምፕ ግን ይህንን  ካደረጉ በኋላ በአሜሪካ እና ሜክሲኮ ድንበር ላይ  የሰፈሩትን ወታደሮች ቁጥር ወደ15 ሺህ ከፍ እንደሚያደርጉ ነው ያስታወቁት። ዘ ኢስት አፍሪካን እንደዘገበው ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *