ትራምፕና ባለቤታቸዉ በኢራቅ ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ
አርትስ 18/04/2011
ሰራዊታቸው በኢራቅ መቆየቱ አክሳሪ እንደሆነ አድርገው በተደጋጋሚ ሲተቹ የነበሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሳይታሰብ ከባለቤታቸ ጋር ያልታሰበ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
ትራምፕ በቱዊተር ገፃቸዉ እኔ እና ሜናሊያ ኢራቅ ውስጥ በሚገኘው ሰራዊታችችን መካከል ስንገኝ የተሰማን ክብር በቃላት የማይገለፅ ነዉ የሚል ፅሁፍ አስፍረዋል፡፡
ፕሬስ ቴሌቭዥን እንደዘገበው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ አልአሳድ በተባለዉ የአየር ማዘዣ ጣቢያ በመገኘት ከወታደሮቻቸው ጋር ውይይቶችን አድርገዋል፡፡
የትራምፕን ድንገተኛ ጉብኝት የኢራቅ ህግ አውጭ አካላት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የጣሰ በማለት አጣጥለውታል፡፡
ምክንያታቸው ደግሞ ትራምፕ ከኢራቅ መንግስት ጋር በቅጡ ሳይነጋገሩ በድብቅ ወደ ሀገራቸው መግባታቸው ነው፡፡
ከኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር መወያየት በአካል ተይዞ የነበረው ለቀጠሮ ተሰርዞ በስልክ እንዲደረግ ከተስማሙ በኋላ ትራምፕ ከባለቤታቸው ጋር በድንገት ኢራቅ መግባታቸው ብዞዎቹን አስቆጥቷል፡፡
ትራምፕ ጦር ሰራዊታቸው ኢራቅ በቆየ ቁጥር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እየበላ ነው ሲሉ እንዳልነበረ አሁንም ጦራቸውን የመቀነስም ሆነ የማስወጣት እቅድ እንደሌላቸው መናገራቸው ለትችት ዳርጓቸዋል ነው የተባለው፡፡
ሶሪያ የነበረዉን ጦራቸውን በድንገት ማስወጣታቸው ባለ ስልጣኖቻቸውን ጭምር ማሰቆጣቱን አስመልክተው አሜሪካ የዓለም ፖሊስ ሆና የመቀጠል ዓላማ የላትም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡