loading
ቤጂንግና ዋሽንግተን ጦርነት እናብርድ እያሉ ነው

ቤጂንግና ዋሽንግተን ጦርነት እናብርድ እያሉ ነው

አርትስ 23/03/2011

በንግድ ሰበብ ወደ ቀዝቃዛው ጦርነት ሊገቡ ጫፍ ላይ ደርሰዋል የሚባሉት አሜረሪካና ቻይና ቢያንስ ለሶስት ወራት አንዱ በሌላው ላይ ታሪፍ ላለመጣል አልያም ለመቀነስ ተስማምተዋል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና የቻይናው አቻቸው ሽ ጂፒንግ በቡድን 20 ሀገራት ስብሰባ ከተሳተፉ በኋላ ነው የተወያዩት፡፡

ትራምፕ ሀገራቸው ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ ለሶስት ወራት ጊዜ እስከ 200 ቢሊዮን ዶላር በሚገመቱ የቻይና ምርቶች  ገበያዋን ክፍት ለማድረግ ዝግጁ ናት  ብለዋል፡፡

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ በበኩላቸው ይህ ታላቅ ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረውን የንግድ ጦርነት ለማርገብ አይነተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም በዚህ መልኩ መነጋገራችን የበለጠ ተቀራርበን ችግሮቻችንን ለመፍታት ያግዘናል ብለዋል፡፡

ከኋይት ሀውስ የወጣው መግለጫ ደግሞ ትራምፕና ሽ የተወያዩበት ጉዳይ ውጤታማ አንደነበር ሁለቱም በአድናቆት መናገራቸውን አትቷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *