loading
ባርሴሎና የኮፓ ዴል ሬይ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ምሽት ከሲቪያ ጋር  ይጫወታል  

ባርሴሎና የኮፓ ዴል ሬይ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ምሽት ከሲቪያ ጋር  ይጫወታል

የኮፓ ዴል ሬይ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ትናንት መካሄድ ጀምረዋል፡፡

ትናንት ምሽት ሜስቲያ ላይ ሄታፌን ያስተናገደው ቫሌንሲያ 3 ለ 1 በማሸነፍ በአጠቃላይ ውጤት 3 ለ 2 በመርታት ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፉን አረጋግጧል፡፡

ሜዳቸው ላይ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን 1 ለ 0 ያሸነፉት ሄታፊዎች በሞሊና የመጀመሪያ ደቂቃ ግብ ቀዳሚ መሆን ቢችሉም፤ ሮድሪጎ በ61ኛው እና በጨዋታው የጭማሪ ደቂቃ ያስቆጠራቸው ተጨማሪ ሁለት ግቦች ሀትሪክ በመስራት ቫሌንሲያን ወደ ግማሽ ፍፃሜው እንዲበቃ አስችሏል፡፤

በምሽቱ ግጥሚያ ሶስት ተጫዋቾች የቀይ ካርድ ሰለባ የሆኑ ሲሆን ዳኮናን እና ጎንዛሌዝ ከሄታፌ እንዲሁም ዲያክቢ ከቫሌንሲያ ከሜዳ ተሰናብተዋል፡፡

ዛሬ ሁለት የሩብ ፍፃሜ የመልስ ግጥሚያዎች የመደረጉ ሲሆን ባለፈው ሳምንት በስታዲዮ ራሞን ሳንቼዝ ፒዡዋን በሲቪያ የ2 ለ 0 ሽንፈት ገጥሞት የተመለሰው የካታላኑ ባርሴሎና ካምፕ ኑ ላይ ምሽት 5፡30 ተጠባቂ ጨዋታውን ከአንዳሉዥያው ሲቪያ ጋር ይከውናል፡፡

ባርሳ ግማሽ ፍፃሜውን ለመቀላቀል ከ 3 ለ 0 በላይ ውጤት ማስመዝገብ የሚጠበቅበት ሲሆን በመጀመሪያው ጨዋታ ሊዮኔል ሜሲ እና ሌሎች የቡድኑን ቁልፍ ተጫዋቾች ያላሰለፉት አሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ፤ የቡድኑን የባለፉት አራት አመታት ስኬት ለማስቀጠል እና ውጤቱን ለመቀልበስ ለጨዋታው ትልቅ ትኩረት ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የመጀመሪያ ግጥሚያቸውን በአንድ አቻ ውጤት ያጠናቀቁት ሪያል ቤቲስ እና ኢስፓኞል በስታዲዮ ቤኒቶ ቪያማሪን ይገናኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *