loading
በጣና ሀይቅ በተሰወረችው ጀልባ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስክሬን ተገኘ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 12፣ 2013 በጣና ሀይቅ በተሰወረችው ጀልባ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስክሬን ተገኘ:: በጣና ሀይቅ በተሰወረችው ጀልባ ህይወታቸው ያለፈ የ7 ሰዎች አስክሬን ተገኘ በማእከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ በጣና ሀይቅ 13 ሰዎችን አሳፍራ በጉዞ ላይ እንዳለች በተሰወረችው አነስተኛ ጀልባ ህይወታቸው ያለፈ የሰባት ሰዎች አስክሬን መገኘቱን ፖሊስ አስታወቀ።

የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ቸርነት አስማረ እንደገለጹት አስክሬኑ የተገኘው በሃይቁ ላይ ላለፉት ሁለት ቀናት በጀልባና በዋናተኞች በተካሄደ አድካሚ ፍለጋ ነው፡፡ አስክሬኑ የጣና ሀይቅ በሚያዋስናቸው በጎርጎራና አዲስጌ ድንጌ በተባለ የገጠር ቀበሌ መካከል በሀይቁ ላይ በማእበል ተገፍተው ዛሬ ንጋት ላይ ተንሳፈው መገኘቱን አስረድተዋል፡፡

የቀሪውን የስድስት ሰዎች አስክሬን ለማግኘት ፍለጋው ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመው የጀልባዋን መስመጥ የሚያጣራ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ምርመራ መጀመሩን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ ጀልባዋ ሐምሌ 9 ቀን 2013 ዓም ሌሊት ድንች የጫኑ 13 ሰዎችን አሳፍራ በወረዳው አዲሰጌ ድንጌ ተብሎ ከሚጠራ ቀበሌ አባን ላይ ጎጥ መነሻዋን በማድረግ ወደ ጎርጎራ ወደብ በጉዞ ላይ እንዳለች መሰወሯ ይታወሳል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *