loading
በጋምቤላ ማረሚያ ቤት በተነሳ ግጭት 92 ታራሚዎች አመለጡ

በጋምቤላ ማረሚያ ቤት በተነሳ ግጭት 92 ታራሚዎች አመለጡ

ጋምቤላ ከተማ ዙሪያ ዞን ማረሚያ ቤት ከተፈጠረው የእርስ በእርስ ግጭት ጋር ተያይዞ 92 ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች አምልጠው መውጣታቸውን ማረሚያ ቤቱ አስታወቀ።

ከማረሚያ ቤቱ የወጡት ታራሚዎች ላይ ክትትል እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

የዞኑ ማረሚያ ቤት አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ጆን ኡሞድ እንደገለጹት በውሃ ምክንያት በሁለት ግለሰቦች መካከል የተነሳ አለመግባባት ሰፍቶ ወደ ግጭት በማምራቱ ከ316 ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች መካከል 92ቱ አምልጠው ወጥተዋል።

ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች ሊያመልጡ የቻሉት በወቅቱ በማረሚያ ቤቱ በቂ የፖሊስ ኃይል ስላልነበረ መሆኑን አሰታውቀዋል።

በግጭቱ በሶስት ሰዎች ላይ ከደረሰው መጠነኛ መቁሰል በስተቀር በህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ረዳት ኢንስፔክተር ጆን ኡሞድ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ከፌዴራልና ከክልል የፀጥታ አካላት አስፈላጊው ኃይል ተጨምሮ የማረጋጋት ስራ በመከናወኑ የተሻለ ሁኔታ መፈጠሩንም ማስታወቃቸዉን ኢዜያን ጠቅሶ ፋና ዘግቧል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *