በጉጉት በተጠበቀው የአመቱ ኮከብ ተጫዋች ምርጫ ሉካ ሞድሪች አንደኛ በመሆን ተመርጧል፡፡
ከአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ጎን ለጎን በተካሄደ የሽልማት ስነ ስርአት፡-
ዴቪድ ቤካም የፕሬዚዳንት ሽልማት ከአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር ተበርክቶለታል፡፡
በኮከብ ግብ ጠባቂነት፡ የሪያል ማድሪዱ ኬይለር ናቫስ ተመርጧል፡፡
በተከላካይ መስመር፡ ሰርጂዮ ራሞስ
በአማካይ መስመር፡ ሉካ ሞድሪች
በአጥቂ ስፍራ፡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በመሆን ተመርጠዋል፡፡
በጉጉት በተጠበቀው የአመቱ ኮከብ ተጫዋች ሉካ ሞድሪች በመሆን ተመርጧል፡፡ በ2013 ፍራንክ ሪቤሪ ኮከብ ከተባለ በኋላ ከሜሲ እና ሮናልዶ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ ሞድሪች በታሪክ ስሙን አስፍሯል፡፡
ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ሞሀመድ ሳላህ 2ኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ሲይዙ
4. አንቶን ግሪዝማን
5. ሊዮኔል ሜሲ
6. ክልያን ምባፔ
7. ኬቨን ዲ ብሩይኔ
8. ራፋኤል ቫራን
9. ኤደን ሀዛርድ
10. ሰርጂዮ ራሞስ
በሴቶች ኮከብ ተጫዋች፡ ፔርኒል ሀርደር በመሆን ተመርጣለች፡፡
አርትስ ስፖርት 24/12/2010